loading
ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡

አዲስ አበባ፣የካቲት 12፣ 2013 ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ተገለፀ፡፡ ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓት በአዲስ አበባ ከተማ ባሉ ሁሉም ሆስፒታሎች ተግባራዊ እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ፡፡ ወ/ሮ አዳነች በየካቲት 12 ሆስፒታል በመገኘት ወረቀት አልባ ዲጂታል የጤና መረጃ አያያዝ ስርዓትን በይፋ ስራ አስጀምረዋል፡፡

በፕሮግራሙም ዛሬ የጀግኖች አርበኞች መታሰቢያ ቀን ለጀግኖች አርበኞች መታሰቢያ ሆስፒል ዉስጥ ቴክኖሎጂዉ መጀመሩ ትልቅ ትርጉም አለዉ ብለዋል፡፡
የካቲት 12 የመጀመርያዉ ን አገልግሎት ቢጀምርም ፤ወደሌሎች ሆስፒታሎች ይህ ስራ እንዲስፋፋ አስተዳደሩ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡ የጤና መረጃ መሰረተ ልማት ፤የሀገራችን የጤና ዘረፍን በብዙ መንገድ ያሻሽላል ያሉት ድገሞ የካቲት 12 ሆስፒታል ሜዲካል ኮሌጅ ፕሮቮስት ዶ/ር አየለ ተሾመ ናቸዉ፡፡

ዲጂታል የወረቀት አልባ የአገልግሎት አሰጣጥ በቴና ዘርፍ የመረጃ አብት በቴናዉ ዘርፍ ለማቀጣጠል ግዛል ብለዋል፡፡ የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዩሐንስ ጫላ የጤና መረጃ ስርዓትን ማዘመን ማለት የጤና ስርዓትን ችግሮች ለመለየትም ሆነ መሰረታዊ ለዉቶችን ለመተግበር ዋና ቁልፍ ነዌ ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *