loading
ዶላር እናበዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችን የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ::

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 ዶላር እናበዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦችን የፌዴራል ፖሊስ በቁጥጥር ስር አዋለ:: በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ዶላር እናባዛለን በማለት የማጭበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ ግለሰቦች በፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ኢንተለጀንስ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገልጿል፡፡

በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው ‘ሲኤምሲ’ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ ዶላር እናባዛለን በማለት የአካባቢውን ህብረተሰብ ሲያጭበረብሩ የነበሩት ኢትዮጵያዊት እና ካሜሮናዊ ዜገነት ያላቸዉ ናቸዉ ተብሏል፡፡ ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር በዋሉበት ሰዓት ዶላር እናባዛለን በማለት ለማጭበርበሪያ የሚጠቀሙባቸው ሁለት ካርቶን ዶላር የሚመስል ወረቀትና ሁለት ጠርሙስ ኬሚካል ይዘው መገኘታቸው ታውቋል፡፡

ከማህበረሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል ኢንተለጀንስ ሁለቱንም ግለሰቦች በቁጥጥር ስር በማዋል በተጠርጣሪዎቹ ላይ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡ እንደነዚህ አይነት ህገ-ወጥ ተግባር በሚፈጽሙ ግለሰቦች ዙሪያ ጥቆማ በመስጠት ህብረተሰቡ እያደረገ ያለውን ድጋፍና ትብብር አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት ፖሊስ ጥሪ ማቅረቡን የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን በማህበራዊ ገፁ ይፋ አድርጓል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *