ጃፓን በ25 ዓመት ታሪኳ ከባድ የተባለው አውሎ ነፋስ ገጥሟታል ፡፡
አርትስ 30/12/2010
ኪዮቶ እና ኦሳካ በተባሉት ከተሞች የሚኖሩ ጃፓናዊያን ታይፎን ጀቢ የሚል መጠሪያ ከተሰጠው አውሎ ነፋስ ጋር እየታገሉ ይገኛሉ፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው እስካሁን በአደጋው 10 ሰወች ሲሞቱ 300 የሚሆኑት ጉዳት ደርሶባቸዋል፡፡
የሀገሪቱ የመንግስት ቃል አቀባይ ዮሺሂድ ሱጋ እናዳሉት አደጋው በተከሰበት አቅራቢያ የሚኖሩ ከ1.2 ሚሊዮን በላይ ዜጎች በፍጥነት አካባቢያቸውን ለቀው ካልወጡ የአደጋው ሰለባ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡
ከ800 ያላነሱ በረራወች በአደጋው ሳቢያ በመሰረዛቸው በርካታ መንገደኞች በአየር ማረፊያዎች መጨውን ሁኔታ በመጠባበቅ ላይ ይገኛሉም ተብሏል፡፡