loading
ጄምኮርፕ ኩባንያ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን አደጋን ለመቀነስ ለሚያደርገዉ ዝግጅት ድጋፍ እያደረኩኝ ነዉ አለ፡፡

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጄምኮርፕ ኩባንያ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን አደጋን ለመቀነስ ለሚያደርገዉ ዝግጅት ድጋፍ እያደረኩኝ ነዉ አለ፡፡
ኩባንያዉ የብሔራዊ የአደጋ መከላከያ እና ዝግጁነት ኮሚሽን 200,000 ሜትሪክ ቶን ስንዴ ለመግዛት ላወጣው ጨረታ ተወዳዳሪ ሆኖ በመገኘት በድጋሚ ማሸነፉን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋልጄምኮርፕ ኢኮኖሚውን በንግድ ሥራ ለመደገፍ እና ኢንቨስት ለማድረግ የኢትዮጵያን ገበያ የተቀላቀለው በ2010ዓ.ም. ሲሆን ከዚያን ጊዜ አንሥቶ 900,000 ቶን ስንዴ እና ከ23 ሚሊየን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት ለኢትዮጵያ የምግብ ገበያ አቅርቧል፡፡
በኢትዮጵያ የጄምኮርፕ ተቋም ሪጅናል ማናጅር የሆኑት አቶ ኮስታስ በመግለጫው ላይ “ላለፉት 18 ወራት ጄምኮርፕ ጠንካራ እና አስተማማኝ የግብርና ምርቶች ንግድ ሥርዓትን በኢትዮጵያ ውስጥ ለመዘርጋት በርካታ ተግባራትን ያከናወነ ሲሆን; በአሁን ሰዓትም ስንዴ እና የምግብ ዘይትን ለመንግሥት እና ለግል አስመጪዎች የማቅረብ ሥራን እያከናወነ ይገኛል፡፡” ሲሉ ገልጸዋል፡፡ጄምኮርፕ በአዲስ አበባ እና በጅቡቲ ውስጥ ቅርንጫፎቹን ከፍቶ መንቀሳቀሱ የሥራውን ኺደት ለማቀላጠፍ፣ ግልጽ የሆነ ተግባቦት እንዲኖር ለማስቻል ከፍተኛ ሚና መጫወታቸዉን በመግለጫዉ አስታዉቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *