loading
ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሸንፏል

ጅማ አባ ጅፋር በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሸንፏል

የ2018/19 የቶታል ካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ወደ ምድብ ድልድል ለመቀላቀል የደርሶ መልስ የመጀመሪያ ጨዋታዎች ተካሂደዋል፡፡

ትናንት የሞሮኮውን ሃሳኒያ ዩኒዬን ስፖርት አጋዲር በአዲስ አበባ ስታዲየም ያስተናገደው ጅማ አባ ጅፋር የ 1 ለ 0 ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ሙሉ ጨዋታው በጣት ከሚቆጠሩ የግብ ሙከራዎች ውጭ ያን ያህል ሳቢ ያልነበረ፤ በሁለቱ ቡድኖች ያን ያህልም ኢላማውን የጠበቀ የግብ ሙከራ ያልተስተዋለበት ነበር ማለት ይቻላል፡፡

በተለይ የጅማው ግብ ጠባቂ ዳንዬል አጃዬ ከእንግዳው ቡድን የሚሰነዘሩ አንዳንድ ኳሶችን በተደጋጋሚ ሲተፋ ተስተውሏል፡፡

ለሃሳኒያ አጋዲር ድል ማድረግ ሚና የነበራትን ግብ በሁለተኛው የጨዋታ አጋማሽ 72ኛው ደቂቃ ላይ ዞሂር ቻውች ማስቆጠር ችሏል፡፡

የጅማው ቡድን በተለይ ጎል ካስተናገደ በኋላ ግብ ለማስቆጠር ጥረት ቢያደርግም ሳይሳካለት ቀርቷል፡፡

ይህን ተከትሎ የሞሮኮው ቡድን በኮንፌዴሬሽን ዋንጫ የምድብ ድልድል መንገዱን ማሰማመር ይዟል፤ በሚቀጥለው ሳምንት የመልሱ ጨዋታ በሞሮኮ አጋዲር ከተማ የሚከናወን ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *