loading
ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘ

ጉምሩክ ባላወጣው ጨረታ አታሎ የጨረታ ማስከበሪያ ለመቀበል የሞከረው ግለሰብ ተያዘ

ነዋሪነቱ አዲስ አበባ የሆነው ይህ ግለሰብ ነጋዴዎችን አነጋግሮ በጉምሩክ ለጨረታ የቀረበ የግንባታ ብረት እንዳለ በማስመሰል አታሎ ገንዘብ ሊቀበል ሲል ጅግጅጋ ላይ ተይዟል።

በጅግጅጋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት የስራ ሃላፊዎች ስም የጨረታ ኮሚቴ ነኝ በማለት ለጨረታ ማስከበሪያ በሚል የሀሰት ማሳመኛ 690 ሺህ ብር ሊቀበል ሲል በቁጥጥር ስር ውሏል።
ግለሰቡ ነጋዴዎችን ለማታለል የሞከረው ለጨረታ የቀረበ 2 ሚሊዮን ሶስት መቶ ሺህ ኪ.ግ የግንባታ ብረት በመኖሩ በአነስተኛ ዋጋ አሸናፊ ትሆናላችሁ በማለት ነው።
ጥርጣሬ ያደረባቸው ነጋዴዎችም ወደ ጅግጅጋ ጉምሩክ በማምራት ለማጣራት ባደረጉት ጥረት ግለሰቡ ሊያዝ ችሏል።
ግለሰቡ ከአዲስ አበባ እስከ ጅግጅጋ ኔትወርክ በመዘርጋት ካልተያዙ ሌሎች ግብረአበሮቹ ጋር በመሆን ነው የማታለል እና የማጭበርበር ድርጊት ሲፈፀም የተደረሰበት።
የጉምሩክ ኮሚሽን ህብረተሰቡ ከአጭበርባሪዎች እንዲጠነቀቅና በተቋማት ስም ክፍያ ሲጠየቅ ከመክፈሉ አስቀድሞ ማረጋገጥ እንዳለበት ጥሪውን አስተላልፏል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *