loading
ጊኒ የኢቦላ ቫይረስ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች።

አዲስ አበባ፣የካቲት 8፣ 2013 ጊኒ የኢቦላ ቫይረስ በወረርሽኝ ደረጃ መከሰቱን ይፋ አደረገች። በጊኒ ደቡብ ምስራቅ በተከሰተው የኢቦላ ወረርሽኝ ለህልፈት ከተዳረጉት ሰዎች ባሻገር አራት ሰዎች ደግሞ ቫይረሱ እንደተገኘባቸው ተነግሯል። በደቡብ ምስራቅ የሀገሪቱ ክፍል በምትገኘው ጎዋኬ በአንድ የቀብር ስነ ስርዓት ላይ የተሳተፉ 7 ሰዎች የማስመለስ፣ የመድማት እና ማስቀመጥ  እንዳጋጠማቸው ተጠቁሟል።

የኢቦላ ቫይረስ የተገኘባቸው እነዚህ ሰዎች አሁን ላይ በለይቶ ማቆያ እንደሚገኙ የጊኒ ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል። የጤና ሚኒስትሩ ሬሜይ ላማህ የሀገሪቱ ባለስልጣናት በኢቦላ በተከሰተው ሞት በእጅጉ እንዳሳሰባቸው መናገራቸውን አልጀዚራ ዘግቧል። በጊኒ ለመጀመሪያ ጊዜ ተከስቶ ከፈረንጆቹ ከ2013 እስከ 2016 የቆየው የኢቦላ ወረርሽኝ በምዕራብ አፍሪካ የ11 ሺህ 300 ሰዎችን ህይወት ቀጥፏል።

አሁን ላይ በሀገሪቱ በተለይ ኢቦላ በተከሰተበት አካባቢ የምርመራ እና ቫይረሱ የተገኘባቸውን ሰዎች የመለየት ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር ገልጿል። የዓለም ጤና ድርጅትም በጊኒ የኢቦላ ወረርሽኝ መከሰቱ እንዳሳሰበው መግለጹም ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *