ግዙፉ የጣልያን ኩባንያ በአፍሪካ የመጀመሪያ ቅርንጫፉን በኢትዮጵያ ከፈተ
አርትስ 12/02/2011
ካልዜዶኒያ የተባለው ግዙፍ የጣልያን የአልባሳት ፋብሪካ በአፍሪካ የመጀመሪያ የሆነውን ፋብሪካውን የመቐለ ከተማ አስመረቀ።
ፋብሪካው ለምፅዋ ወደብ ባለው ቅርበት ለምስራቅ አፍሪካ ምጣኔ ሀብት ዕድገት ጉልህ አስተዋፅዖ እንደሚያበረክት የተገለጸ ሲሆን ለአንድ ሺ ዜጎች የስራ እድል ከመፍጠሩ ባለፈ ለውጭአገራት ከሚያቀርበው ምርቱ እንደ መነሻ በየወሩ 22 ሚሊዮን ብር ገቢ ማስገኘት መጀመሩ ታውቋል ሲል የውጨ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት አስታውቋል።
የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም የፋብሪካውን መመረቅ አስመልክተው የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡