ጎንደርን ፍለጋ የተሰኘ መጽሀፍ ተመረቀ፡፡
በጋዜጠኛ ሄኖክ ስዩም የተጻፈዉ ጎንደርን ፍለጋ የጉዞ ማስታወሻ ትላንት ሲመረቅ በክብር እንግድነት የተገኙት የኢትዮጵያ የቱሪዝም ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰርፀፍሬ ስብሀት እንደተናገሩት ጋዜጠኛ ሄኖክ የጻፈዉ መጽሀፍ ባህልን ታሪክንና ቱሪዝምን የያዘ ነዉ፤ልንጠቀምብት ይገባል ብለዋል፡፡
ጎንደርን ፍለጋ መጽሀፍ ጋዜጠኛዉ በተለያየ አካባቢዎች ባደረጋቸዉ ጉዞዎች የሰማቸዉን ያያቸዉን ታሪኮች አጣርቶ ያስቀመጠበት ነዉ፡፡
በመጽሀፉ ዉስጥ ጎንደርን ፍለጋ በደጃዝማች አያሌዉ ዳና (አያሌዉ ሞኙ ሰዉ አማኙ )፤ደርሰጌ ማርያም ጃናሞራ እና የጻና ቂርቆስ ጉዳዮች ይገኙበታል፡፡