loading
ጎግል ክሮም በቆዩ የኮምፒውተር ፕሮሰሰሮች ላይ መስራት ሊያቆም ነው::
አዲስ አበባ፣የካቲት 5፣ 2013  በአለማችን ላይ በአሁን ወቅት በብሮውዘር የቴክኖሎጂ ዘርፍ በቀዳሚነት የሚሰለፈው ጎግል ክሮም እንደአውሮፓውያኑ ከ2005 በፊት ተሰርተው አሁንም በማገልገል ላይ በሚገኙ የኮምፒውተር ፕሮሰሰሮች ላይ መስራቱን አንደሚያቆም ተነግሯል፡፡ የ Chromium አበልጻጊ ቡድን ከሰሞኑ እንዳስታወቀው x86 CPUs የተሰኘው የቀድሞው ፕሮሰሰር በጎግል ክሮም ላይ ተቀባይነት እንደማይኖረው እና ብሮውዘሩ በቀጣይ ይዞት በሚመጣው ማዘመኛ የትኛውም የኮምፒውተር ፕሮሰሰር ቢያንስ አንኳን (Supplemental Streaming SIMD Extensions 3) SSE3 የተባለውን ሲስተም የማይቀበል ከሆነ ብሮውዘሩ ለመስራት አንደሚቸገር ተነግሯል፡፡
እንደመረጃው ከሆነ ከቴክኖሎጂው ማደግ ጋር ተያይዞ ብዙ ተጠቃሚዎች ዘመናዊ ሃርድዌሮችን ስራ ላይ የሚያውሉ በመሆናቸው ብዙ ተጎጂዎች ይኖራሉ ተብሎ ባይታሰብም ከ15 ዓመት በላይ እድሜ ባላቸው ኮምፒውተሮች ላይ አሁንም ክሮምን የሚጠቀሙ ሰዎች ግን ግልጋሎቱን ላያገኙ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡ የ Chromium አበልጻጊ ቡድን ይዞት ወጣ በተባለው ሰነድ ላይ ከጉዳዩ ጋር ተያያዥ የሆኑ ወስብስብ መረጃዎች በስፋት የተለቀቁ ቢሆንም ከአሁን በኋላ ጎግል ክሮም አንዲሰራ SSE3 ሊደግፍ የሚችል ፕሮሰሰር የግድ አስፈላጊ እንደሚሆን ተነስቷል፡፡
ረዥም ግዜ የቆዩ የኮምፒውተር ፕሮሰሰሮች በጊዜ ሂደት በአንዳንድ ሶፍትዌሮች ላይ ተቀባይነት እንዳይኖራችው የማድረጉ ነገር ትልቅ ምከንያት የሚቀርብበት ባይሆንም አንዳንድ የኮምፒውተር ባለሙያዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን ችግሩ ከእድሜ ጋር የተያያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ አሁን ላይ አንደሚገለፀው እንደአውሮፓውያኑ ከ2000 እስከ 2005 ባሉት አመታት የነበሩት የኮምፒውተር ፕሮሰሰሮች በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እየተተኩ በመምጣታቸው አነዚህን ሃርድዌሮች የሚጠቀሙ ሰዎች በቁጥር እያነሱ መተዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ የኮምፒውተር ፕሮሰሰር አማካይ የሕይወት ዘመን ከ7-10 ዓመት በመሆኑም በአዳደስ መልኩ ከሚበለፅጉት ሶፍትዌሮች ጋር በፍጹም ሊጣጣም ወይም (compatible) ሊሆን አይችልም፡፡ ከዚህ አንፃር ተሻሽለው የቀረቡ የሃርድዌር አማራጮችን በአንድም ይሁን በሌላ መልኩ ጥቅም ላይ ማዋል እጅግ አስፈላጊ ይሆናል፡፡
በዚህ ዘገባ እንደተገለፀው ረዥም ግዜ በቆዩ የኮምፒውተር ፕሮሰሰሮች የሚገለገሉ ተጠቃሚዎች ከዚህ በኋላ የጎግል ክሮም በሃርድዌራቸው ላይ ድጋፍ እንደማይኖረው የሚያሳይ የማስጠንቀቂያ መልእክት የሚደርሳቸው ሲሆን፤ አዲስ ማዘመኛ ያላቸው እንደ Chrome 89 ያሉ ብሮውዘሮች ደግሞ ቆየት ባሉ ሃርድዌሮች ላይ መጫን እንደማይችሉም ተገልጿል፡፡ (TECH-IN)

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *