loading
ጠቅላይ ሚስትር ዐብይ አህመድ ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 23፣ 2012 ጠቅላይ ሚስትር ዐብይ አህመድ ዓለም አቀፉን የሰራተኞች ቀን አስመልክተው መልዕክት አስተላለፉ::

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው ይህ ቀን የዓለም የዓለም ሠራተኞችን ሕይወት የቀየሩ የሠራተኞች ትግሎች የሚታወሱበት ቀን ነው ብለዋል፡፡ይህን ቀን በማሰብ ስለሰራተኛው ማኅበረሰብ ስንነጋገር ስለ ቀጣይዋ ኢትዮጵያ እየተነጋገርን እንደሆነ እናምናለን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ የሀገራችን ጉዞ አምራች ኢንዱስትሪውን ወደ ማስፋፋት እያመራ መሆኑን አውስተዋል፡፡በሠራተኛው እና በአሠሪው መካከል የሚኖረው ግንኙነትም የነገዋን ኢትዮጵያ ታሳቢ ያደረገ ግንኙነት እንዲሆን ተስፋ እንዳላቸውም ገልፀዋል፡፡

የሠራተኞች መብት የማይከበርበት ኢንዱስትሪ ሕይወት አልባ ስለሆነ በሕግና በሞራል የሚመራ፣ የሠራተኛውን መብት ከሀገሪቱ ዕድገትና ከኢንዱስትሪው ሰላም ጋር ያጣጣመ መሆን ይኖርበታል ሲሉም አሳስበዋል፡፡አሠሪዎች የሠራተኞችን መብት ማክበር፣ ጥቅሞቻቸውን መጠበቅ እና መደራጀታቸውን መደገፍ ያለባቸው ለራሳቸው ሲሉ ጭምር መሆኑን በገንዘብ እንደሚገባም ጠቅላይ ሚስትሩ ተናግረዋል፡፡ሀገራችን የገጠማትን የኮሮና ቫይረስ ፈተና በአሸናፊነት ለመወጣት ሁሉም ሰራተኛ የሚችለውን ሁሉ እዲያደርግም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *