loading
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኬንያ እና ሶማሊያን አስታረቁ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ኬንያ እና ሶማሊያን አስታረቁ

በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ሸምጋይነት ኬንያ እና ሶማሊያ በመካከላቸው ያለውን ልዩነት በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ተስማሙ።

የኬንያው ፕሬዚዳንት አሁሩ ኬንያታና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሙሀመድ አብዱላሂ ፋርማጆ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ አደራዳሪነት  በዛሬው ዕለት በኬንያ ውይይት አድርገዋል፡፡

በዚህም በሁለቱ ሀገራት መካከል ለተፈጠረው ውጥረት መንሥኤ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ውይይት በማድረግ በመካከላቸው ያለውን ውጥረት ለመቀነስ የሚያስችሉ እርምጃዎችን ለመውስድ ከስምምነት ላይ መድረሳቸው ነው የተገለፀው።

የሶስቱ ሀገራት መሪዎቹ  ባደረጉት ውይይት ሽብርተኝነትን መከላከል ላይም በጋራ ለመስራት ተስማምተዋል ተብሏል፡፡

በተለይ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ደህነንትን ለማረጋገጥ በትኩረት ለመስራት ነው የተስማሙት።

የሶማሊያ መንግስትም ኬንያና ሶማሊያ በውይይት ልዩነቶቻቸውን እንዲፈቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ላደረጉት አስተዋፅኦ ምስጋና አቅርቧል።

ኬንያ እና ሶማሊያ በባህር ክልል ወሰን ይገባኛል ጥያቄ ሰሞኑን አለመግባባት ውስጥ መግባታቸው የሚታወስ ነው።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *