loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በባሌ ዞን በኩታ ገጠም ማሳ ስንዴ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን ጎበኙ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ በባሌ ዞን በኩታ ገጠም ማሳ ስንዴ የሚያመርቱ አርሶ አደሮችን ጎበኙ

አርትስ 30/03/2011

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ በተደረገው ጉብኝት በተጨማሪ ከአርሶአደሮች ጋር ውይይት ተካሂዷል፡፡ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው በጉብኝቱ ላይ የቀድሞው የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር ቶኒ ብሌየር ተገኝተዋል።

በባሌ ዞን ጊኒር ወረዳ አርዳ ቀብሶ ቀበሌ 2ሺህ350 ሄክታር መሬት ላይ 133 አርሶ አደሮች ያለሙትን የዱረም ስንዴ ማሳ ነው የተጎበኘው።

በጉብኝቱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንንና የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳ  ተገኝተዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *