loading
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ከዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ቦርዤ ብሬንዴ ጋር ከሲውዘርላንድ ዳቮስ የቀጠለ ውይይት አደረጉ።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ዛሬ በጽ/ቤታቸው ከዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ ፕሬዝዳንት ቦርዤ ብሬንዴ ጋር ከሲውዘርላንድ ዳቮስ የቀጠለ ውይይት አደረጉ።

በጥር ወር 2011 እንደተወሰነው ኢትዮጵያ የ2013 የዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ በአፍሪካ እንድታዘጋጅ ተመርጣለች።

በዛሬው እለት ጠ/ሚር አብይ ና ፕሬዝዳንት ቦርዤ  ይህንኑ አሕጉራዊ ጉባኤ ለማካሄድ የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎችንና አግባቦችን የሚያትት ስምምነት ተፈራርመዋል።

የዓለም የኢኮኖሚ ጉባኤ በአፍሪካ በመስከረም ወር 2013 በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ይኖሩታል ተብሎ ይጠበቃል።

ምንጭ ፤-የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *