ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለአፍሪካ ቀን” የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2012 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ “ለአፍሪካ ቀን” የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላለፉ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በእንኳን አደረሳችሁ መልእክታቸው አፍሪካ ባለ ብዙ ፀጋ ባለቤት ናት በመሆኑም የአፍሪካ ቀንን ስናከብር የምንፈልጋትን የአፍሪካን እዉን እንድትሆን አንድነታችንን እናጠናክር ብለዋል::የአፍሪካ ቀን “የአፍሪካ ነፃነት ቀን” እየተባለም የሚከበር ሲሆን እ.ኤ.አ ግንቦት 25 ቀን 1963 በ32 ነፃነታቸውን በተቀናጁ የአፍሪካ ሀገራት አዲስ አበባ ላይ ባደረጉት የመጀመሪያ ጉባኤ እንዲከበር የተወሰነ ቀን ነው። ቀኑ ከዚህ ቀደም በአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት በተለያዩ ሁነቶች ሲከበር የቆየ ቢሆንም እለቱ ዛሬ በቪዲዮ በሚካሄድ ኮንፍረንስ እንደሚታሰብ ህብረቱ አመልክቷል። ይህም የቪዲዮ ኮንፍረንስ “የመሳሪያን ድምፅ ማጥፋት” የሚለውን የዘንድሮው የህብረቱ መሪ ቃል ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር አስተሳስሮ እንደሚወያይበት ታዉቋል፡፡ቀኑን ምክንያት በማድረግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የእንኳን አደረሰን መልዕክት በፌስ ቡክ ገፃቸዉ አስፍረዋል፡፡