loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅመ ደካሞች በቤተ-መንግሥት ማዕድ አጋሩ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 17፣ 2014 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለጎዳና ተዳዳሪዎችና አቅመ ደካሞች በቤተ-መንግሥት ማዕድ አጋሩ:: ጠቅላይ ሚኒስትሩ የትንሳኤን በዓል ምክንያት በማድረግ ጧሪ ለሌላቸው አረጋዊያን፣ የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ በተለያዩ ምክንያቶች ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ህፃናትና ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው በድምሩ 230 ወገኖች ማዕድ አጋርተዋል።
በመርሃ-ግብሩ ላይ የተገኙት ወገኖች በቤተ-መንግሥት ተገኝተን በጠቅላይ ሚኒስትሩ ለተደረገልን ግብዣና መልካም መስተንግዶ እናመሰግናለን ብለዋል።


ማዕድ ተጋሪዎቹ የተቸገረን ሰው መርዳትን የመሰለ መልካም እና ታላቅ ነገር ባለመኖሩ በዓልን በደስታ እንድናሳልፍ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባደረጉልን ነገር ተደስተናል ብለዋል። የትንሳኤ በዓልን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር በቤተ መንግሥት በማሳለፋችን በእጅጉ ተደስተናል ሲሉም አክለዋል። የኢትዮጵያ ሰላም የሁላችንም ሰላም በመሆኑ በአገራችን ዘላቂ ሰላምና መረጋጋት ሰፍኖ ማየት እንሻለን፤ ለዚህም ስኬት ሁላችንም እንትጋ ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል። ኢትዮጵያዊያን የመረዳዳት፣ የመተጋገዝና ለአገር ሰላም አብሮ የመቆም የቆየ እሴታችን ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ሲሉም መልእክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
ዘገባው የኢዜአ ነው

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *