ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ባለቤታቸው የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎት ልማት ማህበርን በገና በዓል ዋዜማ ጎበኙ::
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ እና ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የዘውዲቱ መሸሻ የህፃናትና ቤተሰብ የበጎ አድራጎት ልማት ማህበርን በገና በዓል ዋዜማ ጎበተኝተዋል ::
ለህፃናቱም የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች: ብርድ ልብስና አንሶላ አበርክተዋል::
ዐቢይ አሕመድ የእማማ ዘውዲቱን ጥረት በማድነቅ በየቀን ተቀን እንቅስቃሴያችን የልግስናን ባህል እናዳብር ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል::
በተጨማሪም እማማ ዘውዲቱ የበለጠ ህፃናትን መርዳት እንዲችሉ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እንዲረዷቸው አበረታትተዋል::
የዛሬ 27 አመት የተቋቋመው ማህበሩ ከሁለት መቶ በላይ ተንከባካቢ የሌላቸው ህፃናት መጠለያ ሲሰጥ ቆይቷል::
እማማ ዘውዲቱ በአሁኑ ወቅት 40 በማእከሉ ውስጥና 35 ከማእከሉ ውጭ ያሉ ህፃናት እርዳታ እየሰጡ ይገኛሉ::
በቅርቡ በግማሽ ክፍሉ ላይ የእሳት ቃጠሎ ቢደርስበትም ማእከሉ አገልግሎት መስጠቱን አላቆምም::