loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ደቡብ አፍሪካን ሊጎበኙ ነው፡፡

ኢ.ቢ.ሲ በድረገፁ እንዳስነበበው የቀድሞ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ ከኤስ .ኤ.ቢ.ሲ ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት ዶክተር አብይ አህመድ ከቀጠናው ሀገራት ውጭ በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የሚያደርጉትን ጉብኝት የመጀመሪያው በደቡብ አፍሪካ እንዲሆን ፍላጎት አላቸው፡፡
አቶ ኃይለማርያም ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የተላከ መልዕክት ለደቡብ አፍሪካ ፕሬዝዳንት ሰርል ራማ ፖሳ አድርሰዋል፡፡
በፀረ አፓርታይድም ይሁን በነጻነት ትግል ወቅት ኢትዮጵያ ለአፍሪካውያን ወንድሞቿ አለኝታ ነበረች ያሉት አቶ ኃይለማርያም በኢትዮጵያና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለው ግንኙነት ለአፍሪካ መልካም ትሩፋት እንዳለውም ገልጸዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *