ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ መቱ ከተማ ጎበኙ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ መቱ ከተማ ጎበኙ፡፡
የኤፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ ኦሮሚያ ክልል ኢሉባቦር ዞን መቱ ከተማን ጎብኝተዋል፡፡
በመቱ ከተማ ቆይታቸውም የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከ60 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ለሚያስገነባው ዘመናዊ የምርት መቀበያና ማከማቻ መጋዘን የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል።
የመሰረተ ድንጋዩንም የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ እና የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንድምአገኝ ነገራ ናቸው ያስቀመጡት።
በተጨማሪም በመቱ ከተማ የተገነባውን የአስፓልት መንገድ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በተገኙበት ተመርቆ ለአገልግሎት ይፋ ተደርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በመቱ ከተማ የሚገኘውን ማረሚያ ቤት የገበኙ ሲሆን፥ በማረሚያ ቤቱ ውስጥ የተሰሩ የተለያዩ የአረንጓዴ ልማት ስራዎቸን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድና የኦሮሚያ ክልል ርእስ መስተዳድር አቶ ለማ መገርሳ በመቱ ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው ህብረተሰብ ተወካዮች ጋር ተወያይተዋል።
ፋና እንደዘገበዉ በውይይቱ ላይ የተሳተፉ የህብረተሰብ ተወካዮችም ከመልካም አስተዳደር፣ ከመንገድና ንፁህ የመጠጥ ውሃ ጋር በተያያዘ የመሰረተ ልማት እንዲሁም ከህክምና ጋር በተያያዘ ሆስፒታል ይገንባልን የሚሉ ጥያቄዎችን አንስተዋል።