loading
ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሴባስቲያን ከርዝ ጋር ተወያዩ

ጠቅላይ ሚኒስት ዶክተር አብይ ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሴባስቲያን ከርዝ ጋር ተወያዩ

አርትስ 27/03/2011

  የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ የኦስትሪያ መራሄ መንግስት ሴባስቲያን ከርዝን በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት ግንኙነት እና በዓለም አቀፍ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መረጃ ያመለክታል።

መራሂ መንግስቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት የክብር አቀባበል ተደርጎላቸዋል።

ሰባስቲያን ከርዝ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ጠ/ሚር ዐቢይ  ከኦስትሪያ መራሄ መንግስት የሆኑት ሴባስቲያን ኩርዝ ጋር ያደረጉት የሁለትዮሽ ዉይይት የንግድ፣ የኢንቨስትመንት እና የቴክኖሎጂ ልውውጦችን በማጠናከር ላይ ያተኮረ ነበር።

የዲፕሎማሲ ግንኙነቱንም የበለጠ ለማጠናከር፣የኢትዮጵያ ኤምባሲ በቪየና ስለመክፈትም ተነጋግረዋል።.

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *