loading
ጠ/ሚ ዐቢይ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ላቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቀረቡ::

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 11፣2013 ጠ/ሚ ዐቢይ በወታደራዊ ማሰልጠኛዎች ዝግጅቶችን ላቀረቡ የኪነጥበብ ባለሙያዎች ምስጋና አቀረቡ::ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ መቼም፣ የትም፣ በምንም በሚል መሪ ቃል፣ የብሔራዊ ቴአትር፣ ኦሮሞ የባህል ማዕከልና የአዲስ አበባ ቴአትር ቤቶች የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች በወታደራዊ ማሠልጠኛዎች ተገኝተው ዝግጅቶችን አቅርበዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በትዊተር ገጻቸው ላይ ባሰፈሩት መልዕክት÷ኪነ ጥበብ ምንጊዜም ከኢትዮጵያ ጀግንነት ጋር ናት ብለዋል፡፡ በዚህም ዝግጅቶቹን ላቀረቡ የኪነ ጥበብ ባለሞያዎች ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን÷ሌሎች ከያንያንም አርአያነታቸውን እንደሚከተሉ ተስፋ አደርጋለሁ ብለዋል

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *