loading
ጠ/ሚ ዐቢይ ከጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ዲፕሎማሲያዊ ፋይዳ

አዲስ አበባ፣ ጥር 5፣ 2014 ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ከጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት በዲፕሎማሲው አውድ መሻሻሎች
የመኖራቸው ማሳያ ነው ሲል -የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ፡፡ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ጋር ያደረጉት የስልክ ውይይት ከዚህ ቀደም የነበረውን የግንኙነት መንፈስ እየተቀየረ ለመሆኑ ማሳያ መሆኑን ገልፀዋል።


ጠቅላይ ሚኒስትሩ በህግ ማስከበሩ ዘመቻ ዙሪያ ማብራሪያ መስጠታቸውን የገለፁት አምባሳደር ዲና ፥ የሰብአዊ መብት አያያዝ ፣ የሰብአዊ ድጋፍ ማቅረብ እና በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን መልሶ ማቋቋም ጋር የተገናኙ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን አንስተዋል። ከዚህ ቀደም የተስተዋለውን በጥርጣሬ የተቃኘ አካሄድ ለመለወጥ ለንግግር ዝግጁ መሆናቸውን ማሳየታቸውን እና በጋራ ጉዳዮች ላይ አብረው ለመስራት መስማምታቸውንም ገልጸዋል።


በዚህም የፓለቲካ ዲፕሎማሲ ምህዳሩ መንፈስ እየተቀየረ መምጣቱ እና ግንኙነትን በማጠናከር ረገድም ውጤታማ ስራ እንዲሰራ መንገድ የሚፈጥር መሆኑን አንስተዋል። በአንድ በኩል የህልውና አደጋውን ለመቀልበስ በተደረገው ዘመቻ የተገኘው ድል፣ በሌላ በኩል ብሄራዊ መግባባትን ለማምጣት የተጀመረው ሂደት በኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን የበረታ ትግል የእስካሁኑ ጫና ትርጉም ያጣ እንዲሆን አድርገዋል ብለዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *