loading
ፈረንሳይ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰብ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነች::

አዲስ አበባ፣ መስከረም 21፣ 2013 ፈረንሳይ በሩዋንዳ የዘር ማጥፋት ወንጀል የተከሰሱ ግለሰብ ለዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት ተላልፈው እንዲሰጡ ወሰነች:: የፈረንሳይ ከፍተኛ ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤት ፌሊሲን ካቡጋ የተባሉ በዘር ጭፍጨፋው ወቅት ጥቃት አድራሾቹን በመሳሪያ እና በሌሎች ቁሳቁሶች ይደግፉ እንደነበር በማረጋገጡ ነው ተላልፈው እንዲሰጡ የወሰነው፡፡ አልጀዚራ እንደዘገበው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አቃቤ ህግ ሰውየውን የከሰሳቸው ዘር ማትፋጽን በገንዘብና በቁሳቁስ መደገፍ በሚል ወንጀል ነው፡፡

በወቅቱ በሩዋንዳ በቡናና ሻይ ኢንቨስትመንት ተሰማርተው የነበሩት እኝህ ባለ ሃብት እንደ አወሮፓዊያኑ አቆጣር በ1994 በሀገሪቱ በ100 ቀናት ውስጥ ከ800 ሺህ በላይ ቱትሲዎች ሲጨፈጨፉ ከፍተኛውን ሚና ተጫውተዋል ነው የተባለው፡፡ ካቡካ በሩዋዳ የመንግስት ለውጥ መደረጉን ተከትሎ ወደ ፈረንሳይ ተሰደው ለዓመታት ተደብቀው ከቆዩ በኋላ ነው የተያዙት፡፡ ሩዋንዳ የ87 ዓመቱ የቀድሞው ባለሃበት ለሰሩት የዘር ጭፍጨፋ ወንጀል በሀገራቸው ፍርድ ቤት
እንዲዳኙ እንደምትፈልግ ተናግራለች፡፡ የተከሳሹ ጠበቆች ደንበኛቸው በዕድሜ በመግፋታቸው ለበሽታ ተጋላጭ በመሆናቸው በተለይ ከኮሮናቫይረስ ስጋት እንዲርቁ የውጭ ጉዞ እንዳያደርጉና ባሉበት ሀገር ጉዳያቸው እንዲታይ ጠይቀዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *