loading
“ፈጠራ በቀውስ ጊዜ” የአዲስ ወግ ዌቢነር ውይይት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሄደ::

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 20፣ 2012 “ፈጠራ በቀውስ ጊዜ” የአዲስ ወግ ዌቢነር ውይይት በቪዲዮ ኮንፈረንስ ተካሄደ::

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አዘጋጅነት በተካሄደዉ ዉይይት  በቀውስ ጊዜ የሚፈጠሩ አዳዲስ ችግሮችን ማለፍ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ አተኩሯል፡፡ችግር ለፈጠራ መንስኤ በመሆኑ ችግር ፈቺ ፈጠራዎች ላይ ትኩረት ሊደረግ እንደሚገባ የቪዲዮ ኮንፈረንሱ አወያይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ ዶክተር አብርሃም በላይ ተናግረዋል።ሁሉም ስብሰባዎች በቪዲዮ ኮንፈርንስ እንዲደረጉ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትሩ፤ ውይይቶች በቪዲዮ ኮንፈረንስ አማካይነት እየተካሄዱና በቀጣይ የበለጠ ተጠናክረው እንዲቀጥሉ የሚደረግ መሆኑን አመልክተዋል።

ኢትዮጵያ ወደ ዲጂታል ኢኮኖሚ እንድትሸጋገር የሚያግዙ የፖሊሲና የህግ ማዕቀፍ እንዲጸድቅ እየተሰራ እንደሆነም ጠቁመዋል።የኢ-ኮሜርስ፣ ኢ-ሰርቪስ፣ የኢ፤ትራንዛክሽን አዋጅ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቆ ለህዝብ ተወካዮች መላኩንም ተናግረዋል።እነዚህን አገልግሎቶች በፍጥነት ስራ ላይ ለማዋል እየተሰራ ሲሆን ከ30 በላይ በቴክኖሎጂ ላይ የሚሰሩ ተቋማት ያላቸውን የቴክኖሎጂናአማራጭ እንዲያቀርቡ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።የመንግስት ተቋማትን እናአገልግሎት ፤ሰዎች በያሉበት ሆነው ለማግኘት እንዲችሉ “የኢ-ሰርቪስ” አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችል ስራ እየተሰራ ይገኛል ብለዋል።የኮሮናቫይረስን ለመከላከል የሚያስችል የፈጠራ ስራ እየሰሩ ያሉ ሰዎች ለሚኒስቴሩ እንዲያቀርቡ እና እውቅና እንዲያገኙ ሁኔታዎች መመቻቸቱንም ጠቁመዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *