loading
ፌስቡክ ከ8 ሚሊዮን በላይ የህጻናት እርቃን ምስሎችን አስወገደ

ፌስቡክ ከ8 ሚሊዮን በላይ የህጻናት እርቃን ምስሎችን አስወገደ

አርትስ ስፖርት 16/02/2011

ፌስቡክ በሦስት ወራት ዉስጥ 8 ነጥብ 7 ሚሊዮን እርቃናቸውን የሚታዩ የሕጻናትን ምስል አስወግጃለሁ አለ፡፡

ፌስቡክ እንዳስታወቀዉ  ሕጻናትን የተመለከቱ ጾታዊ ግንኙነት ቀስቃሽ ምስሎችን እንደተለቀቁ ማስወገድ የሚችል አዲስ ሶፍትዌር ተፈጥሯል፡፡
ሶፍትዌሩ አገልግሎት ላይ የዋለው ባለፈው ዓመት ቢሆንም ለሕዝብ ይፋ የሆነው በቅርቡ ነው፡፡

እንደ ፌስቡክ ገለጻ አዲሱ ሶፍትዌር ከሕጻናት ጋር የተያያዙ የፆታዊ ትንኮሳዎችን የሚያሳዩ መረጃዎችን ማወቅ የሚችል ነው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበዉ እንዲወገዱ ከተደረጉት ስምንት ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ምስሎች ውስጥ 99 በመቶ ያህሉ የፌስቡክ ተጠቃሚዎች ዘንድ ከመድረሳቸው በፊት ነው ከገጹ የተነሱት፡፡

ፌስቡክ የጥላቻና የዘረኝነት ቅስቀሳ ይዘት ያላቸውን መልዕክቶችም የሚያስወግድ አሠራር እንደሚዘረጋ አስታውቆ ነበር፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *