loading
ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ በሌሎች ባለስልጣናት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፈቀደ

ፍርድ ቤቱ አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ በሌሎች ባለስልጣናት ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀን ፈቀደ

አርትስ 19/02/2011

የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 19ኛ የወንጀል ችሎት አቶ አብዲ መሀመድ ዑመርን ጨምሮ የክልሉ የቀድሞ ከፍተኛ ባለስልጣናት፥ በተጠረጠሩበት የማፈናቀል፣ የአካል ጉዳትና ህይወትማለፍ ወንጀል ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን ፈቅዷል።

አንደ ፋና ዘገባ መርማሪ ፖሊስ ቀሪ ስራዎችን ለማከናወን ተጨማሪ የ10 ቀን የጠየቀ ሲሆን፥ ተጠርጣሪዎቹ ተቃውሞ አቅርበዋል።

ተጠርጣሪዎቹ ፖሊስ በተደጋጋሚ ጊዜ ለተመሳሳይ ምርመራ በየጊዜው ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ አይደለም ሲሉ ተቃውሞ አሰምተዋል።

ጉዳዩን የተከታተለው ፍርድ ቤቱም ለፖሊስ ተጨማሪ 10 የምርመራ ቀን በመፍቀድ ለጥቅምት 29 ቀን 2011 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *