loading
ፒያሳ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይዎት ሲያልፍ አስር ሰዎች ለአካል ጉዳት ተዳረጉ

ፒያሳ አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይዎት ሲያልፍ አስር ሰዎች ለአካል ጉዳት ተዳረጉ

አርትስ 27/02/2011

ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ፒያሳ ቸርችል ጎዳና አካባቢ በደረሰ የመኪና አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ እና 10 ሰዎች ለአካል ጉዳት መደረጋቸው ተሰምቷል፡፡

አደጋው ዛሬ ማለዳ 12 ሰዓት ከ30 አካባቢ መድረሱን እና በወቅቱ ከፒያሳ ወደ ለገሃር ይጓዝ የነበረ ሚኒ ባስ ታክሲ ቼርችል ጎዳና ጋር ያለ የትራፊክ መብራት ጋር ሲደርስ ከ ቪ8 መኪና ጋር ተጋጭቶ  እንደሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል፡፡

በአደጋው የአንድ ሰው ህይዎት ሲያልፍ፥ በ10 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድና ቀላል ጉዳት መደረሱን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎችም በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኙ የተለያዩ ሆስፒታሎች የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ይገኛል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *