loading
ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ላይ የቀረበው የክስ ሀሳብ ውድቅ ሆነ

ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ላይ የቀረበው የክስ ሀሳብ ውድቅ ሆነ

አርትስ 03/04/11

ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ሞሃመድ እንዲጠየቁና እንዲከሰሱ በሶማሊያ ምክር ቤት 92 አባላት የቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በቂ ድጋፍ ባለማግኘቱ ውድቅ ሆኗል።

ይኸው የሆነው በፕሬዚዳንቱ ላይ ጥርጣሬ አለን ብለው ሀሳቡን ካቀረቡት 92 አባላት መካከል 14ቱ ራሳቸውን በማግለላቸው መሆኑን የምክር ቤቱ ፅህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

14ቱ የፓርላማ አባላት ስማቸው በስህተት መካተቱንና በፕሬዚዳንቱ ላይ የቀረበውን የክስ የውሳኔ ሃሳብ እንደማይደግፉት ተናግረዋል።

የውሳኔ ሀሳቡ ፕሬዚዳንት ሞሃመድ አብዱላሂ ከኢትዮጵያና ኤርትራ ጋር ሚስጥራዊ ስምምነት በመፈራረም፣ ዳኞችን እና ወታደራዊ አዛዦችን በግላቸው ውሳኔ በመሾም የሀገሪቱን ህገመንግስት ጥሰዋል የሚል ክስ የያዘ ነው፣  ቢቢሲ እንደዘገበው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *