loading
ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአቶ ሙስጠፌ ሞሐመድ እና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር በአካባቢው በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ተወያዩ።

አዲስ አበባ፣ የካቲት 2፣ 2014 ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ከአቶ ሙስጠፌ ሞሐመድ እና ከክልሉ ኃላፊዎች ጋር በአካባቢው
በተከሰተው ድርቅ ዙሪያ ተወያዩ። ፕሬዚዳንቷ ከ.ተ.መ.ድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሞሐመድና የልዑካን ቡድናቸው ጋር በመሆን
በሶማሌ ክልል ጉብኝት አድርገዋል።


በቀብሪ በያ ባደረጉት የመስክ ጉብኝት በድርቁ የተነሳ ከተፈናቀሉት ወገኖች ጋር ተገናኝተዋል። የአካባቢው ሕዝብ ለተጎዱት ወገኖቹ የመጀመርያ ደራሽ በመሆን ላሳየው ታላቅነት እንዲሁም የክልሉ መንግሥት እያደረገ ላለው ጥረትም ምስጋና አቅርበዋል፡፡ በድርቁ ለተጎዱት የመጀመርያ እርዳታ እንደተጠበቀ ሆኖ በዘላቂነት ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው መመለስ እንደሚገባም ገልጸዋል፡፡

በተያያዘም ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ በዛሬው እለት የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት ኦሊሴጎን ኦባሳንጆን ጨምሮ ሌሎች ልዑካንን አስከትለው ሰመራ መግባታቸው ተሰምቷል፡፡ ሰመራ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሃንፈሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የሃገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች አቀባበል አድርገውላቸዋል። ፕሬዚዳንቷ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *