ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ህዝበ ውሳኔ ድል ከቀናቸው ስልጣናቸውን እስከ 2036 የማራዘም እድል ይኖራቸዋል ተባለ::
አዲስ አበባ ፣ሰኔ 17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን በመጭው ህዝበ ውሳኔ ድል ከቀናቸው ስልጣናቸውን እስከ 2036 የማራዘም እድል ይኖራቸዋል ተባለ::ሩሲያ በፈረንጆቹ ጁላይ 1 ላይ ህገ መንግስት ለማሻሻል የህዝበ ውሳኔ ምርጫ ልታካሂድ በዝግጅት ላይ ትገኛለች፡፡ በህዝበ ውሳኔው መሰረት ህገ መንግስቱ ይሻሻል የሚለው ድምፅ የሚያሸንፍ ከሆነ ፑቲን ተጨማሪ ሁለት የምርጫ ውድድሮችን ለማድረግ የሚያስችላቸው እድል ይፈጠርላቸዋል ተብሏል፡፡
በዚህም መሰረት ሁለቱን ምርጫዎች ተወዳድረው የሚያሸንፉ ከሆነ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠት እስ 2036 ድረስ በስልጣን ላይ ይቆያሉ ማለት ነው፡፡
ዩሮ ኒውስ እንደዘገበው ይህን የፑቲንን ህገ መንግስት የመሻሻል ሀሳብ ብዙዎቹ ቢቃወሙትም በመጨረሻ ለህዝብ ውሳኔ ቀርቦ ጊዜውን እየጠበቀ ነው፡፡
ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን የሩሲያዊያንን ህይዎት በመለወጡ ረገድ ተሳክቶላቸዋል ተብለው የሚወደሱትን ያህል ስልጣን አብዝተው ይወዳሉ በሚልም በሰፊው ይታማሉ፡፡