loading
ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከአርብ ጀምሮ በአማራ ክልል ጉብኝት ያደርጋሉ

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ከአርብ ጀምሮ በአማራ ክልል ጉብኝት ያደርጋሉ

አርትስ 29/02/2011

 

የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ በአማራ ክልል ጉብኝት ሊያደርጉ መሆኑ ተነግሯል።

ፕሬዚዳንት ኢሳያስ ዓርብ ጎንደር ከተማ የሚገቡ ሲሆን፥ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን ጨምሮ የአማራ ክልል ከፍተኛ ባለስልጣናት አቀባበል እንደሚያደርጉላቸው ተነግሯል።

ፕሬዚዳንቱ በክልል በሚኖራቸው ቆይታም በጎንደር እና አካባቢው የሚገኙ ታሪካዊ የቱሪስት መስህብ ቦታዎችን እና የልማት ስራዎችን እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል።

የጎንደር ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ፅህፈት ቤት ለጋዜጠኞች እንዳስታወቀው ለሶስተኛ ጊዜ ኢትዮጵያ የሚገኙት የፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ጉብኝት በሃገር ደረጃ የተጀመረውንግንኙነትያጠናክረዋል።

የአማራ ክለል ባለስልጣናት ወደ ኤርትራ ተጉዘው ተመሳሳይ ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *