loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዳዲስ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸው ተሰማ::

አዲስ አበባ፣ጥር 24፣ 2013 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት አዳዲስ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸው ተሰማ:: የቀድሞው ፕሬዚዳንት በስልጣን ላይ በነበሩበት ወቅት ህግ ተላልፈዋል መባላቸውን ተከትሎ ክስ ስለሚጠብቃቸው ራሳቸውን ለመከላkል ነው ይህን ያደረጉት ተብሏል፡፡ ትራምፕ ከሚጠብቃቸው ክስ ይከላከሉልኛል ያሏቸውን ዴቪድ ሾን እና ብሩስ ካስቶር የተባሉ የህግ ጠበቆችን መቅጠራቸውን ይፋ አድርገዋል፡፡

ትራምፕ አዳዲስ ጠበቆችን ለመቅጠር የተገደዱት የቀድሞዎቹ ጠበቆቻቸው ከሳቸው ጋር ለመስራት ፍላጎት ሳይኖራቸው ቀርቶ ስራቸውን በመልቀቃቸው መሆኑ ተሰምቷል፡፡ ትራምፕ የሚከሰሱት ደጋፊዎቻቸው የካፒቶልን ህንፃ እንዲወርሩ ጥሪ አስተላልፈዋል በሚል ሲሆን በወቅቱ የተካሄደው አመፅ ለአምስት ሰዎች ህይዎት ማለፍ ምክንያት ሆኗል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው 45 የሚሆኑ የሪፓብሊካን የምክር ቤት አባላት የትራምፕ የክስ ሂደት እንዳይቀጥል ጥረት ቢያደርጉም በአብላጫ ድምፅ ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡

የቀድሞው ፕሬዚዳንት መከሰሳቸው እውን መሆኑን በተገነዘቡ ጊዜ ደግሞ ትራምፕ ራሳቸውን ለመከላከል በቂ የዝግጅት ጊዜ እንዲያገኙ ክሱ እንዲዘገይ ጠይቀዋል፡፡ ትራምፕ በምርጫ አልተሸነፍኩም ስልጣኔንም አላስረክብም በማለት ከፍተኛ ውዝግብ ካስነሱ በኋላ በባይደን በዓለ ሲመት ላይ ሳይገኙ ዋይት ሀውስን ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *