ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::
አዲስ አበባ፣ሐምሌ17፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህገ ወጥነትን ለመከላከል በርካታ የፌደራል ሀይሎችን አሰማራለሁ አሉ ::ፕሬዚዳንቱ ከፎክስ ኒውስ ጋር በስልክ ባደረጉት ቃለ ምልልስ እስከ 75 ሺህ ወታደሮችን በሁሉም የአሜሪካ ከተሞች ለማሰማራት እቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡ይሁን እንጂ ይህን የምናደርገው ከየግዛቶቹ የድጋፍ ጥያቄ ከቀረበልን ነው ያሉት ትራምፕ አግዙን የሚሉን ከሆነ ያለማቅማማት እናደርገዋለን ብለዋል፡፡ የጆርጅ ፍሎይድን ግድያ ተከትሎ በመላ ሀገሪቱ የተቀሰቀሰው ተቃውሞ ስጋት የፈጠረባቸው ፕሬዚዳንቱ የፌደራል የፀትታ ወኪሎችን ማሰማራትን የመጨረሻ አማራጭ አድርገው እንዲመለከቱ አድርጓቸዋል ተብሏል፡፡ ሲ ኤን ኤን እንደዘገበው ትራምፕ ሀሳባቸው በአካባቢው ባለስልጣንት ተቀባይነት ባይኖረውም የፌደራል ህግ አስከባሪዎችን ወደ ሺካጎ እንልካለን ብለዋል፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ የአሜሪካ የፍትህ ተቋም በፖርትላንድ፣ ኦሬጎን እና ዋሽንግተን የፌደራል ፖሊሶች ያልተመጣጠነ ሀይል ተጠቅመዋል በሚል ምርመራ መጀመራቸው ተሰምቷል፡፡