loading
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህግ ለማያከብሩ ከተሞች ከፌደራል የሚመደብላቸውን ፈንድ እንደሚያቋርጡ አሰጠነቀቁ::

አዲስ አበባ፣ነሐሴ 28፣ 2012 ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ህግ ለማያከብሩ ከተሞች ከፌደራል የሚመደብላቸውን ፈንድ
እንደሚያቋርጡ አሰጠነቀቁ:: ፕሬዚዳንቱ ሲያትል ፣ ፖርትላንድ ፣ ኒው ዮርክ እና ዋሽንግተን ከተሞችን በስም ጠቅሰው ህግ
የማያከብሩ ከሆነ ከፌደራል የሚደረግላቸው የገንዘብ ድጋፍን እንደሚቆም የሚያስገነዝብ የውስጥ ማስታወሻ መፈረማቸው ተሰምቷል፡፡

በኔ አስተዳደር ከግብር ከፋዮች የሚሰበሰብ ዶላር ህገ ወጥ ትን ለማጠናከር አይባክንም ያሉት ትራምፕ እነዚህን ከተሞች ህገ ወጥነት የተንሰራፋባቸው ዞኖች ብለዋቸዋል፡፡ ሮይተርስ እንደዘገበው ትራምፕ በማስታወሻቸው የሀገሪቱ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዊሊያም ባርን በአመፅ ንብረት እንዲወድም የሚፈቅዱ እና ምክንያታዊ እርምጃዎችን ለመውሰድ ፈቃደኛ ያልሆኑ ባለስልጣናትን ዝርዝር እንዲያዘጋጁላቸው አዘዋል፡፡ የዋይት የበጀት ዳይሬክተር ሩሴል ቮውትም በ30 ቀናት ውስጥ እነዚህን ከተሞች በተመለከተ መመሪያ እንዲያዘጋጁ ትእዛዝ ደርሷቸዋል ነው የተባለው፡፡

የኒውዮርኩ አስተዳዳሪ አንድሪው ኩሞ በቱይተር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ ፕሬዚዳንቱ የተወሰኑ ከተሞችና ግዛቶችን በጀት በመከልከል ኮሮናቫይረስን በአግባቡ እንዳይከላከሉ እንቅፋት እየሆኑ ነው ሲሉ ተችተዋል፡፡ ኩሞ አክለውም እራስን እንደንጉስ መቁጠርና በህዝብ ላይ ፈላጭ ቆራጭ መሆን ህገ ወጥነት ነው በማለት ትራምፕን አጥብቀው ወቅሰዋል፡፡ ትራምፕ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት በተጠቀሱት ከተሞች በጆርጅ ፍሎይድ ግድያ ሳቢያ የተቀሰቀሰው አመፅ አለመብረዱን ተከትሎ ነው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *