ፕሬዝደንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በአፍሪካና አውሮፓ ህብረት ፎረም ላይ ለመሳተፍ ወደ ኦስትሪያ ተጓዙ
አርትስ /08/2011
በነገው ዕለት የሚካሄደው ፎረም በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ላይ ትኩረት ሰጥቶ ይነጋገራል።
ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ በቆይታቸው በፎረሙ ላይ ኢትዮጵያ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ለማስፋፋት በምታካሂዳቸው ተግባራት ላይ ትኩረት ያደረገ ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ከዚህ በተጨማሪ ከተለያዩ ሀገራት መሪዎችና በአለም አቀፍ ደረጃ ታዋቂ ከሆኑ ኩባንያ ሀላፊዎች ጋር ዉይይት ያደርጋሉ ሲል ኢቢሲ ዘግቧል።