loading
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢቫንካ ትራምፕን አነጋገሩ

ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ ኢቫንካ ትራምፕን አነጋገሩ
ፕሬዝደንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ በኢትዮጵያ የሁለት ቀናት ጉብኝት ለማድረግ አዲስ አበባ የምትገኘውን የአሜሪካውን ፕሬዝደንት ልጅ ኢቫንካ ትራምፕን ዛሬ ተቀብለው አነጋግረዋል፡፡
ውይይታቸውም የሴቶችን እኩልነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚደረጉ ስራዎች ላይ ትኩረት ያደረገ ነው፡፡

ኢቫንካ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በአለም ላይ እስከ 2025 ድረስ 500 ሚሊዮን ሴቶችን ተጠቃሚ የሚያደርግ ኢኒሽየቲቭ ይፋ ማድረጋቸውን አስታውሳለች ፡፡ ይህ ባለፈው የካቲት ይፋ የተደረገው ፕሮግራም በሶስት መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩር የገለጸችው ኢቫንካ ፤የሴቶችን አቅም ማጎልበት፤ የሴቶችን የሥራ ፈጣሪነት እድል ማስፋትና ለሴቶች አጋዥ የሆኑ ህጎችና ደንቦችን ማጠናከር የሚሉት የፕሮግራሙ ማጠንጠኛዎች እንደሆኑ ነው በማብራራሪየዋ ያመለከተችው፡፡
ከዚህም አንጻር በኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት የሚከናወኑ ተግባራት የሚደነቁ መሆኑን የጠቀሰችው ኢቫንካ ትራምፕ ይህን ሂደትም አሜሪካ በተለያየ መንገድ እንደምትደግፈው ተናግራለች፡፡ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ በሁሉም መስክ የተያያዘችውን የለውጥ ሂደትም አስደናቂ ብለዋለች፡፡
በፕሬዝደንትትራምፕየተቀረጸውናበአለምላይያሉሴቶችንለመደገፍያለመውኢንሽየቲቭጥሩእርምጃመሆኑንየገለጹትፕሬዝደንትሣህለወርቅዘውዴፕሮግራሙሴቶችንማዕከልእስካደረገናከፍወዳለደረጃየሚያሸጋግርእስከሆነድረስተቀባይነትየሚኖረውነውብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሴቶችን አቅም ለማጎልበት በአዲስና በተለየ የለውጥ አቅጣጫ እየተንቀሳቀሰች መሆኑን አንስተው በተለይም ሴቶች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ከገቡ በኋላ የሚያጋጥሟቸውን ችግሮች በመፍታት ትምህርታቸውን በስኬት ጨርሰው እንዲወጡ ለማድረግ በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ትኩረት መደረጉን ነው ያብራሩት፡፡

በሴቶች ዙሪያ ከሚሰሩ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችንም ጋር በመቀናጀት የተሻለ ስራ መፈጸም የሚቻልባቸው ጉዳዮችም ላይ በስፋት እንደሚሰራበት ፕሬዝዳንቷ ተናግረዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *