loading
ፕሬዝዳንትአልበሽር ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

ፕሬዝዳንት አልበሽር ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

ከወራት በፊት በህዝባዊ አመፅ ተገፍተው ከስልጣናቸው የወረዱት የቀድሞው የሱዳን ፕሬዝዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር ፍርድ ቤት የቀረቡት ሀገራቸው ከሳቸው አገዛዝ በኋላ የሲቪል መንግስት ለመመስረት የሚያስችል ስምምነት ባደረገች ማግስት ነው፡፡

አልበሽር ክስ የተመሰረተባቸው በሙስና፣በርካታ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን በቤታቸው እና በቢሯቸው በማከማቸት እንዲሁም ያልተገባ ስጦታ በመቀበል ወንጀል ነው ተብሏል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው አቃቤ ህግ ህገ ወጥ ገንዘብን ህጋዊ አስመስሎ በመጠቀም ወንጀል ጥርጥሯቸው ሌላ ምርመራ ከፍቶባቸዋል፡፡

አልበሽር ፍርድ ቤት ከመቅረባቸው ቀደም ብሎ አመንስቲ ኢንተርናሽናል የተባለው የሰብዓዊ መብት ተቋም ፕሬዝዳንቱ ለፍርድ መቅረባቸው ጥሩ ሆኖ ሳለ አሁንም በሱዳን ህዝብ ላይ የፈፀሙት ወንጀል መጣራት አለበት የሚል አስተያየት መስጠቱ ይታወሳል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *