loading
ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡

አዲስ አበባ ፣ ሃምሌ 19፣ 2013  ፕሮፌሰር አንቶኒ ፋውቺ አሜሪካ ኮቪድ-19 ወረርሽኝን ለመከላከል የምትሄድበት መንገድ ስህተት ነው አሉ፡፡ ፕሮፌሰሩ ከሲ ኤን ኤን ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ በመላው አሜሪካ በርካታ በቀላሉ ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች አሁንም ክትባት አላገኙም ብለዋል፡፡ ይሄ ደግሞ የበሽታውን ስርጭት ለማሰፋት ዋነኛ መንስኤ ይሆናል ነው ያሉት ፕሮፌሰር ፋውቺ፡፡

አዲሱን የቫይረስ ዝርያ ስርጭት የሥርጭት ሁኔታ ስናስተውል ሙሉ ክትባት ባልወሰዱ ሰዎች አሁንም ፈጣን ነው ብለዋል፡፡ 50 በመቶ የሚሆኑት አሜሪካዊያን ሙሉ ክትባት አላገኙም ያሉት የተላላፊ በሽታዎች ኤክስፐርቱ እነዚህ ሰዎች በተለይ ለአዲሱ የዴልታ ቫይረስ በቀላላ እደሚጠቁ አሳስበዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አሜሪካዊያን ክትባቱን እዲወስዱ በተደጋጋሚ ጥሪ ቢያቀርቡም መልእክቱን ተቀብለው ተግባራዊ የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር አናሳ ነው ተብሏል፡፡ክትባቱ በብዛት ባልተሰጠባቸው የአሜሪካ ግዛቶች ቫይረሱ በፍጥነት እየተሰራጨ መሆኑን የጤና ባለሙያዎች ይናገራሉ፡፡ይህ ክስተት ከታየባቸው ግዛቶች መካከል ፍሎሪዳ፣ ቴክሳስ፣ ሚዙሪ የሚገኙበት ሲሆን እነዚህ ግዛቶች 40 በመቶ የሚሆነውን አዲስ የሥርጭት መጠን ይይዛሉ ነው የተባለው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *