loading
ፖፕ ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያስተላለፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡

አዲስ አበባ፣ መጋቢት 22፣2012  ፖፕ ፍራንሲስ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ያስተላለፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉ አስታወቁ፡፡ሊቀ ጳጳስ ፍራንሲስ አንቶኒዮ ጉቴሬዝ ለዓለም ያስተላፉትን የተኩስ አቁም ጥሪ እንደሚደግፉት ተናግረው በዚም ዓለም በሙሉ አቅሟ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን እንድትከላከል ያስችላታል ብለዋል፡፡

በዓለም እየተካሄዱ ያሉ ጦርነቶች የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ  በሚደረግ ጥረት ላይ ከፍተኛ ተጽእኖ የሚፈጥሩ በመሆናቸው የዋና ጸሐፊው ጥሪ ሊከበር ይገባል ብለዋል፡፡ጣሊያን ከ97 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተውባት አሜሪካንን በመከተል ሁለተኛዋ ከፍተኛ በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ያሉባት ሀገር ሆናለች፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሶሪያ፣ የመንና ሊቢያ ያለው ጦርነት እንዲያበቃ ጥረት እያደረገ ሲሆን፤ ጎን ለጎንም በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ንጹሃን የሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ ላይ ነው፡፡

ጉቴሬዝ የጦርነት ቀጠና የሆኑ ሀገራት የጤና ስርዓታቸው እጅግ የወደቀ መሆኑን ተናግተረው ያላቸው ጥቂት የጤና ባለሙያዎች ቁጥር ከዚህ በበለጠ እንዳያሽቆለቁል አስጠንቅቀዋል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *