loading
10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

10 ሚሊዮን ብር የሚገመት ልዩ ልዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ያቤሎ፣ ሀረርና ጅግጅጋ አካባቢዎች ግምታዊ ዋጋው 10 ሚሊዮን ብር የሆነ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በፌዴራል ፖሊስና በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ያቤሎ አካባቢ 9.4 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ የሆኑ ተንቀሳቃሽ ስልኮች፣ መድኃኒት፣ ስኳርና ሌሎች ዕቃዎችን በተሸከርካሪዎች ሲጓጓዝ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሦስት ግለሰቦች ተጠርጥረው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሆነ የሞያሌ ጉምሩክ መቆጣጠሪያ ቅርንጫ ጽ/ቤት አስታውቋል፡፡
የገቢዎች ሚኒስቴር እንዳስታወቀዉ ግምታዊ ዋጋቸው 520 ሺህ ብር የሚደርስ የግንባታ ብረትና ምግብ ነክ የሆኑ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ወደ ጅግጅጋ እና ሀረር ለማስገባት ሲሞከር በፌዴራል ፖሊስ አባላትና በጉምሩክ ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *