loading
11ኛው የአፍሪካ ህብረት የመሪዎች ስብሰባ በአዲስ አበባ ተጀምሯል

አርትስ 08/03/2011

በህብረቱ አዳራሽ የመክፈቻ ሥነ ስርዓቱ ሲካሄድ ከ44 በላይ

የአገር መሪዎች ተገኝተዋል። ጠ/ሚኒስትር አብይ አህመድ አፍሪካ አለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንድትሆን በአንድ ድምፅ ማስተጋባት ይገባል ብለዋል። በኤርትራ ላይ የተጣለው ማዕቀብ መነሳት ለምስራቅ አፍሪካ ሰላም ወሳኝ መሆኑንም አንስተዋል። በዚህ አስቸኳይ ስብሰባ ለአህጉሪቱ ጠቃሚ ውሳኔዎች እንደሚተላለፉ ያላቸውን እምነት ገልፀዋል።

የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ለተፈጠረው ሰላም መሪዎቹን በይፋ አመስግነዋል።

ዛሬና ነገ የሚካሄደው ስብሰባው  የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽንን በማሻሻል እና  ህብረቱን ከእርዳታ ጥገኝነት ለማውጣት በሚቻልባቸው የፋይናንስ ጉዳዮች ላይ ትኩረት  ያደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *