13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ::
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 2፣ 2013 13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ አላማ ቀን ተከበረ::13ኛው ብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን “ሰንደቅ ዓላማችን ለሰላማችን፣ ለአብሮነታችንና ለሃገራዊ ብልጽግናችን!” በሚል መሪ ቃል ተከብሯል፡፡የሰንደቅ ዓላማ ቀኑ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ አርበኞች እና ሌሎች እንግዶች በተገኙበት ነው የተከበረዉ፡፡
ቀኑ በየዓመቱ የተለያየ መሪ ቃል እየተቀረፀለት በፌደራል፣ በክልልና በሁለቱ ከተማ አስተዳደሮች በዋናነት ስለሰንደቅ ዓላማ ምንነት፣ ውክልና እና ትርጓሜ እንዲሁም አዋጁን የሚያብራሩ ሰነዶች እየቀረቡ በሰፋፊ የሕዝብ ንቅናቄ መድረኮች ሲከበር መቆየቱ ተገልጿል፡፡እንዲሁም ሰንደቅ ዓላማ በመስቀልና ወቅታዊ ለውጡን በሚያስቀጥሉ እንዲሁም ከሰንደቅ ዓላማ መርሆዎች ጋር በተገናዘበ አግባብ በየተቋማቱ በመላው ሃገሪቱ ተከብሯል፡፡
የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በተሻሻለው በሰንደቅ ዓላማ አዋጅ ቁጥር 863/2006 ዓ/ም አንቀጽ 2 መሰረት በየዓመቱ ጥቅምት ወር በገባ በመጀመሪያው ሳምንት ሰኞ እንዲከበር መደንገጉ ይታወሳል፡፡