13ኛዉ የህወሃት ድርጅታዊ ጉባዔ ተጠናቀቀ
አርትስ 21/01/2011
ከባለፈው ረቡዕ ጀምሮ በመቀሌ ሲካሄድ የቆየው 13ኛ የህዝባዊ ወያነ ሃርነት ትግራይ /ህወሃት/ ድርጅታዊ ጉባዔ የአቋም መግለጫ በማውጣት ዛሬ ተጠናቋል።
በጉባዔው 55 የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላት እና 11 ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መርጦ፣ ነባር አመራሮችን ሸኝቶ፣ ሊቀመንበር ደ/ር ደብረጺዮን ገ/ሚካኤል እና ምክትል ሊቀመንበር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚያብሄርን መርጦ እንዲሁም ሌሎች ውሳኔዎች አስተላልፎ ነው ዛሬ የተጠናቀቀው፡፡
በጉባኤው ማጠናቀቂያ የህወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ባደረጉት ንግግር አዲሱ አመራር ለትግራይ ክልል ልዩ ትኩረት በመስጠት ለክልሉ የዴሞክራሲ እና የልማት ጥያቄ መመለስ እንደሚሰራ ቃላቸውን ሰጥተዋል፡፡
ህገመንግስታዊ የፌደራል ስርዓቱን ለመጠበቅ ከሌሎች አካላት ጋር በጋራ እንሰራለን ያሉት ሊቀመንበሩ ጉባዔው በጉዳዮች ላይ ክርክርና ትግል የተካሄደበት ድርጅቱን ወደ ውጤታማነት የሚመሩ እቅጣጫዎች የተቀመጡበት ለሀገር የሚጠቅም ውሰኔዎች የተላለፈበት እንደነበረም ገልፀዋል።