loading
13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ቅዳሜና እሁድ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየት ይቀጥላል፡፡

13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ቅዳሜና እሁድ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየት ይቀጥላል፡፡

በሳምንቱ መጀመሪያ የተከፈተዉ 13ኛዉ አዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል ከ500 የዓለማችን ፊልሞች ዉስጥ 60ዎችን በመመረጥ በተለያዩ ቦታዎች ለፊልም አድናቂያንና ባለሞያዎች እያሳየ ነዉ፡፡

ከ60 የተመረጡ ፊልሞች ዉስጥ  24ቱ የኢትዮጵያ ፊልሞች ሲሆኑ፤ከነዚህ ዉስጥ 10 ስሩ የአጭር አጭር የሚባሉ ከ1 ደቂቃ አስከ 5 ደቂቃ የሚፈጁ ፊልሞች  መሆናቸዉን የአዲስ ፊልም ኢንተርናሽናል ፌስቲቫል አስተባባሪ ቤዛዊት ዳምጠዉ ለአርትስ  ቲቪ ተናግራለች ፡፡

ለፊልም ባለሞያዎች ስራቸዉን ማሳያ ቦታ እድል የሚፈጥረዉና ከአለም የፊልም ባለሞያዎች ልምድ ለመቅሰም መድረክ የሆነዉ  ፌስቲቫሉ ዘንድሮም እንደ እቅዱ የተለያዩ ፊልሞችን በማሳየትና የፊልም ጥበብ ማሳደግ ላይ ያተኮሩ ወርክሾፖችን እያካሄደ መሆኑንም ከፊልሙ ፊስቲቫል አስተባባሪ ሰምተናል ፡፡

በፊስቲቫሉም የፊልም ገበያ  በዓለም አቀፍና ሀገርዉስጥ፤የፊልም ታሪክ ነገራና ዝግጅት ሳቢነት፤አለምአቀፍ ኢንቨስቲጌቲቭ ፊልሞችን እንዴት መስራት ይቻላልና በኢንዱስትሪ ዉስጥ የሴቶች ሚናና የሚደርስባቸዉ ተጽእኖ እንዲሁም አጫጭር ፊልሞችን እንዴት  ለገበያ ማዋል ይቻላል የሚሉ ጉዳዩች   ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቦ ዉይይት እየተደረገባቸዉ ነዉ፡፡

ፊልሞቹ በሀገር ፍቅር ቲያትር  በቫምዳስ ኢንተርቴመንት በብሄራዊ   የጣልያን ባህል ማዕከል ፤በአልያንስ ኢትዮ ፍራንሲስ  በብሄራዊ ቤተመጻህፍትና  ወመዘክር  ኤጀንሲ እና በሀገር ፍቅር እየታዩ ሲሆን፤ ቅዳሜና እሁድ ከሚታዩ ፊልሞች መካከል ቁራኛዬ በጣሊያን ባህል ማዕከል ቅዳሜ 12 ሰዓት  እንደሚታይም ከአዘጋጆቹ አርትስ ማወቅ ችሏል፡፡

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *