loading
1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል አርብ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ካልሆነ ግን እሁድ ይከበራል፡፡

1441ኛው የኢድ አል-ፊጥር በዓል አርብ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ  ካልሆነ ግን እሁድ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታዉቋል፡፡
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ኢድሪስ ለምእመናን የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት አስተላልፈዋል፡፡ በዕለቱ የጀምዓ ሶላት እንደማይኖር የገለጹት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ምእመናን በዓሉን በየቤታቸው እንዲያከብሩት አሳስበዋል፡፡  ምእመናን በዓሉን የተራቡትን በማጉረስ፣ የተጠሙትን በማጠጣት በአጠቃላይ የተቸገሩትን በመርዳት እንዲያከብሩም ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *