17ኛው የአርብቶ አደሮች በዓል በጂንካ ከተማ ሊከበር ነው።
17ኛው የአርብቶ አደሮች በዓል በጂንካ ከተማ ሊከበር ነው
የኢትዮጵያ የአርብቶ አደሮች በዓል “የአርብቶ አደሩ የላቀ ተሳታፊነትና ተጠቃሚነት ለአገራዊ አንድነት” በሚል መሪ ቃል በጂንካ ከተማ እንደሚከበር ተገለጸ።
ከጥር 15 እስከ 17 የሚከበረው ይኸው በዓል በደቡብ ክልል አዘጋጅነት በደቡብ ኦሞ ዞን ጂንካ ከተማ እንደሚካሄድም የሰላም ሚኒስቴር ገልጧል፡፡
ዘርፉ በሚፈለገው ደረጃ እንዳያድግ ምክንያት ከሆኑት ውስጥ የማስፈፀም ብቃት ማነስ፤ በዘርፉ የሚሰሩ መንግስታዊና የሲቪክ ተቋማት ያለመናበብ፤ በአርብቶ አደሩ መካከል ውሃንና የግጦሽ መሬትን ምክንያት አድርጎ የሚነሳ ፀብ ይገኙበታል ተብሏል።
እንደኢቢሲ ዘገባ በበዓሉ የአርብቶ አደሩ ክፍል የሚተዋወቅበት፣ የሚመክርበትና ልምድ የሚለዋወጥበት እንደሚሆን ይጠበቃል ፡፡
መንግስት ዘርፉን ለመደገፍ ተጨማሪ 450 ሚሊዮን ብር የበጀት ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል፡፡