19 ክትባት ለሚከተቡ ሰዎች የአንድ ሚሊዮን ዶላር ሎተሪ::
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 12፣ 2013 የኮቪድ ኦሃዮ በተሰኘችው አሜሪካዋ ክፍለ ሃገር የኮቪድ 19 ክትባት ለሚከተቡ ሰዎች አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ የሎተሪ ቁጥር እንደሚሰጣቸው ከተገለፀ በኋላ የተከታቢዎች ቁጥር በእጅጉ መጨመሩ ተገለፀ:: የኦሃዮ ክፍለ ሃገር አስተዳዳሪ ማይክ ዲዋይን በክትባቱ ላይ ጥርጣሬ ያላቸውን ሰዎች ለማበረታታትና የሚከተቡ ሰዎችን ቁጥር ለመጨመር ለእያንዳንዱ ክትባቱን የተከተበ ሰው አንድ ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ የሎተሪ ቁጥር እንደሚሰጥ ያስታወቁት ከሣምንት በፊት ነበር።
በዚህም ምክኒያት በትላንትናው ዕለት፣ ባለፉት ሦስት ሣምንታት ከተከተቡት ሰዎች ቁጥር የበለጡ ሰዎች በአንድ ቀን ውስጥ ክትባቱን መውሰዳቸው ተነግሯል።የተለያዩ የአሜሪካ ክፍላተ-ሃገራት ክትባቱን የሚሸሹ ሰዎችን ለማደፋፈርና ለማበረታታት የተለያዩ አጓጊ ጥቅማጥቅሞችን በመስጠት ሕዝባዊ የኮቪድ መከላከል አቅም እንዲመጣ ለማደረግ በመሞከር ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። የኦሃዮ ክፍለሃገር ባሳለፍንው አርብ ዕለት ብቻ ሃያ አምስት ሺህ አራት መቶ አዳዲስ ተከታቢዎችን መከተብ የቻለ ሲሆን፣ የክፍለ ሃገሩ አስተዳዳሪ አንድ ሚሊዮን ብር የሚያስገኝ የሎተሪ ዕድል ቁጥር እንደሚሰጥ ካስታወቁ በኋላ የተከታቢዎች ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እንደመጣ ለማወቅ ተችሏል።
ይህ የሎተሪ ሃሳብ የመጣው በኤክስፐርቶች ጥናት መሠረት ሕዝባዊ የኮቪድ መከላከል አቅም ወይም ኸርድ ኢሚዩኒቲ ላይ ለመድረስ ቢያንስ 70% ሕዝቡ ክትባቱን መውሰድ እንዳለበት ከተገለፀ በኋላ ነበር። በአሁኑ ወቅት 124 ሚሊዮን አሜሪካውያን ሙሉ በሙሉ ክትባቱን የወሰዱ ሲሆን፣ ይኼም ከጠቅላላ
የአሜሪካ ሕዝብ 38% ማለት ነው። 60 ከመቶ የሚሆኑት ደሞ ቢያንስ የመጀመሪያ ደረጃ ክትባት የወሰዱ መሆኑ የዘጋርዲያን ዘገባ ያመለክታል፡፡