196 ተማሪዎች የፈጠራ ስራዎቻቸውን እያቀረቡ ነው
አርትስ 28/02/2011
የትምህርት ሚኒስቴር ከስቴም ሲነርጂ ጋር በመተባበር ያዘጋጀው የፈጠራ ስራ ውድድር በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እየተካሄደ ነው፡፡
ተወዳዳሪ ተማሪዎቹ የትምህርት ሚኒቴር እና ስቴም ሲነርጂ በሀገሪቱ ከሚገኙ 14 ማዕከላቱ የመለመሏቸው ናቸው፡፡
የፈጠራ ስራዎቹ ለውድድር ቀርበው ከተገመገሙ በኋላ ሽልማትና እውቅና ይሰጣቸዋል፡፡
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አጋር የሆነው ስቴም ሲነርጂ የፈጠራ ስራዎች ወደ ምርት እንዲገቡ የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡