loading
25 ሺህ ዶላር የሚያሸልም የኢኖቬቲቭ ቢዝነስ ሞዴልና ቴክኖሎጂ ያፈለቁ ኢንተርፕራይዞች የሚያወዳድር ፕሮግራም ሊካሄድ ነዉ፡፡

አዲስ አበባ፣ሐምሌ23፣ 2012  25 ሺህ ዶላር የሚያሸልም የኢኖቬቲቭ ቢዝነስ ሞዴልና ቴክኖሎጂ ያፈለቁ ኢንተርፕራይዞች የሚያወዳድር ፕሮግራም ሊካሄድ ነዉ፡፡የፌደራል አነስተኛና መካከለኛ ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማስፋፊያ ባለስልጣን ለአርትስ በላከዉ መግለጫ እንዳስታወቀዉ ፤ ባለስልጣኑ የኢኖቬቲቭ ቢዝነስ ሞዴልና ቴክኖሎጂ ያፈለቁ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የማወዳደር ፕሮግራሙ ከጃፓን አለም አቀፍ ትብብር ኤጀንሲ ጃይካ ጋር በአጋርነት ያዘጋጀዉ ነዉ፡፡

ባለስልጣኑም የፈጠራ ባለሞያ ዎችን ዉድድር ምዝገባ መጀመሩንም አስታዉቋል፡፡በዉድድሩም አሸናፊ ለሚሆኑ ኢንትርፕራይዞች ለእያንዳንዳቸዉ አስከ 25 ሺህ የአሜሪካን ዶላር የሚደርስ ሽልማት ተዘጋጅቷል፡፡ስለፕሮጀክቱ አላማ የመወዳደሪያ መስፈርትና ሌሎችም መረጃዉችም ከጃይካ ድረገጽ ማግኝት እንደሚቻል እና ምዝገባዉም እስከ ነሀሴ18 ድረስ እንደሚካሄድ ባለስልጣኑ በላከዉ መግለጫ አስታዉቋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *