loading
29ኛው የግንቦት 20 በዓል በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል ::

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 20፣ 2012 29ኛው የግንቦት 20 በዓል በዛሬው እለት በመላው ሀገሪቱ በመከበር ላይ ይገኛል :: የግንቦት 20 የድል መታሰቢያ በዓልን በማስመልከትም በዛሬው እለት በአዲስ አበባ መድፍ ተተኩሷልጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድም 29ኛው የግንቦት 20 በዓልን በማስመልከት ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ እንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባስተላለፉት መልዕክት ግንቦት 20 የዘመናዊት ኢትዮጵያን ታሪክ ከቀየሩ ዕለታት አንዱ ነው ብለዋል።ኢትዮጵያን ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ እና ሰላማዊ ለማድረግ አያሌ ታጋዮች እጅግ ውድ የሆነውን ህይወታቸው ሰውተዋል ሲሉም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ የገለፁት።የግንቦት 20 ታጋዮች የነፍስ ዋጋ የከፈሉለት ዓላማ ግፍና ጭቆና፣ አድሎና ወገንተኝነት ቆሞ፤ እኩልነት፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነት፣ ፍትሐዊ ተጠቃሚነትና የጋራ ብልጽግናን ለማረጋገጥ መሆኑን በመልዕክታቸው አንስተዋል።ግንቦት ሃያን ማክበር ያለብን እነዚህን ዓላማዎች እያሰብን መሆን አለበት ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ቀኑን የምናስበው በግንቦት ሃያ ላይ ተቸክለን ሳይሆን ወደፊት እየሄድን የኋላውን እየገመገምን መሆን አለበትም በማለት አሳስበዋል፡፡

ግንቦት ሃያን ያመጡ ታጋዮች ዓላማ ኢትዮጵያን ወደ ግንቦት ሃያ ሁለት መውሰድ እንጂ ወደ ግንቦት አሥራ ዘጠኝ መመለስ አልነበረምም ነው ያሉት፡፡ሀገራቸው በሁሉም መመዘኛ ግንቦት ሃያን አልፋ ግንቦት ሃያ አንድንም ተሻግራ ወደ ግንቦት 22 መድረስ ነበር ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህ ማለትም ሀገራችን ከነበረችበት አስከፊ ሁኔታ ማላቀቅ ብቻ ሳይሆን መድረስ ወደነበረባት የላቀ ደረጃ ማድረስ መሆኑን አስታውሰዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *